\v 21 ኃጢአተኛውም ካደረጋት ኃጢአት ሁሉ ቢመለስ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም። \v 22 የበደለው በደል ሁሉ አይታሰብበትም በሠራው ጽድቅ በሕይወት ይኖራል።