\v 10 እርሱም ቀማኛና ደም አፍሳሽ ልጅ ከዚህም ሁሉ አንዳቸውን የሚያደርገውን ቢወልድ፥ \v 11 እርሱም ጻድቅ አባቱ የሠራውን ሁሉ ባይሠራ በተራራምላይ ባሉ የጣዖት አምልኮ ስፍራ ላይ ቢበላ የባልንጀራውንም ሚስት ቢያረክስ፥