am_ezk_text_ulb/16/35.txt

1 line
789 B
Plaintext

\v 35 ስለዚህ፥ ጋለሞታ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሚ! \v 36 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከውሽሞችሽና ከአጽያፊ ጣዖታትሽ ጋር ባደረግሽው ግልሙትና አማካኝነት ክፉ ምኞትሽን በማፍሰስሽና ኀፍረተ ሥጋሽንም በመግለጥሽ እንዲሁም ለጣዖታትሽ በሰጠሻቸው በልጆችሽ ደም ምክንያት፥ \v 37 እነሆ፥ ከእነርሱ ጋር ደስ ያለሽን የወደድሻቸውንም ውሽሞችሽና የጠላሻቸው ሁሉ ከሁሉም አቅጣጫ በአንቺ ላይ እንዲነሱ እሰበስባቸዋለሁ። እራቁትነትሽን እንዲያዩ በፊታቸው ኀፍረተ ሥጋሽን እገልጣለሁ።