am_ezk_text_ulb/16/09.txt

1 line
570 B
Plaintext

\v 9 በውኃም አጠብሁሽ ከደምሽም አጠራሁሽ በዘይትም ቀባሁሽ። \v 10 በወርቅ የተንቆጠቆጠ ልብስም አለበስሁሽ ከቆዳ የተሰራ ጫማ አደረግሁልሽ፤ በጥሩ በፍታ አስታጠቅሁሽ በሐርም ከደንሁሽ። \v 11 በጌጥም አስጌጥሁሽ በእጅሽም ላይ አንባር በአንገትሽም ላይ ድሪ አደረግሁልሽ። \v 12 በአፍንጫሽም ቀለበት በጆሮሽም ጕትቻ በራስሽም ላይ የክብር አክሊል አደረግሁ።