\v 7 ፊቴንም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ ከእሳትም ይወጣሉ፥ እሳት ግን ይበላቸዋል ፊቴንም በእነርሱ ላይ ባደረግሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። \v 8 ዓመፅን አድርገዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር!"