|
\v 22 ነገር ግን፥ እነሆ! ከወንዶችና ሴቶች ልጆች ጋር የሚያመልጡ ቅሬታዎች ይተርፉላታል። እነሆ! ወደ እናንተ ይወጣሉ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ በኢየሩሳሌምም ላይ ስላመጣሁት ቅጣት በምድሪቱም ላይ ስላመጣሁባት ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ ። \v 23 መንገዳቸውንና ሥራቸውን ባያችሁ ጊዜ ያጽናኑአችኋል ያደረግሁባትንም ሁሉ በከንቱ እንዳላደረግሁባት ታውቃላችሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። |