am_ezk_text_ulb/14/12.txt

1 line
635 B
Plaintext

\v 12 የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። \v 13 የሰው ልጅ ሆይ፥ ምድር በማመፅ በእኔ ላይ ኃጢአት ብትሠራ፥ እኔም እጄን ብዘረጋባት የእንጀራዋንም በትር ብሰብር ራብን ብሰድድባት ሰውንና እንስሳውንም ከእርስዋ ባጠፋ፥ \v 14 እነዚህም ሦስት ሰዎች፥ ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብም፥ በመካከልዋ ቢገኙ እነርሱ በጽድቃቸው ሊያዱኑ የሚችሉት የገዛ ነፍሳቸውን ብቻ ነበር፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፦