am_ezk_text_ulb/13/17.txt

1 line
600 B
Plaintext

\v 17 አንተም፥ የሰው ልጅ ሆይ፥ ከገዛ ልባቸው ትንቢት በሚናገሩ በሕዝብህ ሴቶች ልጆች ላይ ፊትህን አድርግ ትንቢትም ተናገርባቸው፥ \v 18 እንዲህም በል፣ 'ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ነፍስን ለማጥመድ በመላ እጆቸው የጥንቆላ መከዳ ለሚሰፉ ለራሶቻቸውም የተለያየ መጠን ያላቸው ሽፋን ለሚሠሩ ሴቶች ወዮላቸው! የሕዝቤንም ነፍስ ብታጠምዱ በውኑ ነፍሳችሁን ታድናላችሁን?