\v 15 በመዓቴም ግንቡንና ገለባ በሌለው ጭቃ የመረጉትን ሰዎችአጠፋለሁ። ግንቡም ሆነ መራጊዎቹ የሉም እላችኋለሁ። \v 16 እነርሱም ስለ ኢየሩሳሌም ትንቢት የሚናገሩ የሰላምን ራእይ የሚያዩላት የእስራኤል ነቢያት ናቸው። ሰላምም የለም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር"