am_ezk_text_ulb/13/10.txt

1 line
670 B
Plaintext

\v 10 በዚህም ምክንያት ሰላም ሳይኖር "ሰላም ነው!" እያሉ ሕዝቤን መረን ሰደዋል፣ ገለባ በሌለበት ጭቃ የተመረገ ቅጥር ይገነባሉ። \v 11 ቅጥሩን ገለባ በሌለበት ጭቃ ለሚመርጉት ሰዎች እንዲህ በላቸው 'ቅጥሩ ይወድቃል፤ የሚያሰጥም ዝናብ ይዘንባል፥ ቅጥሩኔ ለማፍረስ ታላቅም የበረዶ ድንጋይ እልካለሁ፥ እንዲያደቀውም ዐውሎ ነፋስን እልካለሁ። \v 12 እነሆ፥ ግንቡ በወደቀ ጊዜ። የመረጋችሁት ጭቃ ወዴት አለ? አይሉአችሁምን?