|
\v 8 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ ውሸት ስለተናገራችሁ ጌታ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ የሚናገረው ይህ ነው፡ \v 9 እጄም ከንቱ ራእይን በሚያዩ፥ የውሸት ትንቢት በሚናገሩ ነቢያት ላይ ይሆናል። እነርሱም በሕዝቤ ጉባኤ ውስጥ አይገኙም፥ በእስራኤልም ቤት መዝገብ ላይ አይጻፉም፥ ወደ እስራኤልም ምድር አይገቡም እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ! |