am_ezk_text_ulb/12/14.txt

1 line
692 B
Plaintext

\v 14 ሊረዱትም በዙሪያው ያሉትን ሁሉና ወታደሮቹን ሁሉ በየእቅጣጫው እበትናቸዋለሁ፣ከኋላቸውም ሰይፍ እልክባቸዋለሁ። \v 15 በአሕዛብም መካከል በበተንኋቸው ጊዜ፥ በአገሮችም በዘራኋቸው ጊዜ፥ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ። \v 16 ነገር ግን በሚሄዱባቸውም አሕዛብ መካከል ርኵሰታቸውን ሁሉ እንዲመዘግቡ ከሰይፍና ከራብ ከቸነፈርም ጥቂቶች ሰዎችን ከእነርሱ አተርፋለሁ፣ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።