am_ezk_text_ulb/12/11.txt

1 line
757 B
Plaintext

\v 11 ደግሞም፦ እኔ ምልክታችሁ ነኝ እኔ እንዳደረግሁ እንዲሁ ይደረግባቸዋል፥ እነርሱም በስደት ወደ ምርኮ ይሄዳሉ በላቸው። \v 12 በመካከላቸውም የሚኖረው አለቃ ንብረቱን በጫንቃው ላይ ተሸክሞ ግንቡን ፈንቅሎ በጨለማ ይወጣል። ንብረታቸውን ለማውጣት ግንቡን ይፈነቅላሉ። አለቃውም በዓይኑ ምድሪቱን እንዳያይ ፊቱን ይሸፍናል። \v 13 መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ከለዳውያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል።