\v 8 በነጋታውም የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። \v 9 "የሰው ልጅ ሆይ፥ ዓመፀኛው የእስራኤል ቤት ' የምታደርገው ምንድር ነው?' ብለው ጠየቁህን? \v 10 አንተም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ይህ ትንቢታዊ ጉዳይ በኢየሩሳሌም የሚኖረውን አለቃና በመካከላቸውም የሚኖሩትን የእስራኤል ቤትን ሁሉ የሚመለከት ነው' በላቸው።