\c 11 \v 1 መንፈስም አነሣኝ ወደ ምስራቅ መውጫ ወደሚመለከት ወደ እግዚአብሔር ቤት ምሥራቅ በር አመጣኝ። እነሆም፥ በበሩ መግቢያ ሀያ አምስት ሰዎች ነበሩ፥ በመካከላቸውም የሕዝቡን አለቆች የዓዙርን ልጅ ያእዛንያንና የበናያስ ልጅ ፈላጥያን አየሁ።