am_ezk_text_ulb/10/09.txt

1 line
710 B
Plaintext

\v 9 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ በኪሩቤል አጠገብ አራት መንኰራኵሮች ነበሩ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ፥ አንዱ መንኰራኵር በአንዱ ኪሩብ አጠገብ ነበረ። የመንኰራኵሮቹም መልክ እንደ ቢረሌ ድንጋይ ነበረ። \v 10 የአራቱም መልክ አንድ ይመስል ነበር፥ መልካቸውም በመንኰራኵር ውስጥ እንዳለ መንኰራኵር ነበረ። \v 11 ሲንቀሳቀሱም ወደየትኛውም አቅጣጫ ይሄዱ ነበር፤ ፊት ለፊት ስለሚሄዱ ሲሄዱ አይገላመጡም ነበር። ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር።