am_ezk_text_ulb/10/01.txt

1 line
549 B
Plaintext

\c 10 \v 1 ከዚያም በኪሩቤል ራስ ላይ ወደ ነበረው ጠፈር ተመለከትኩ። በላያቸው እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ እንደ ዙፋን የሚመስል መልክ ተገለጠ። \v 2 እግዚአብሔርም በፍታም የለበሰውን ሰው " በመንኰራኵሮች መካከል ከኪሩብ በታች ግባ፥ ከኪሩቤልም መካከል ካለው እሳት ፍም እጆችህን ሙላ በከተማይቱም ላይ በትነው" አለው። ሰውዬውም እያየሁት ገባ።