am_ezk_text_ulb/09/01.txt

1 line
617 B
Plaintext

\c 9 \v 1 ከዚያም "ጠባቂዎች የሚያጠፋ መሣሪያን በእጃቸው ይዘው ወደ ከተማይቱ ይቅረቡ" ብሎ በታላቅ ድምፅ በጆሮዬ ጮኸ። \v 2 እነሆም፥ እያንዳንዳቸው አጥፊውን መሣሪያ በእጃቸው ይዘው ስድስት ሰዎች በሰሜን አቅጣጫ ካለው ከላይኛው በር በኩል መጡ፣ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰ የጸሐፊም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።