am_ezk_text_ulb/06/08.txt

1 line
777 B
Plaintext

\v 8 ነገር ግን ቅሬታዎችን አስቀራለሁ፣ እናንተ በየአገሩ ስትበተኑ ከአህዛብ መካከል ከሰይፍ የሚያመልጡ ይኖራሉ። \v 9 እነዚያ ያመለጡትም በምርኮ አገር ሆነው ከእኔ ዘወር ካለው አመንዝራ ልባቸውና ወደ ጣዖታቶቻቸው ከሚያየው አመንዝራ ዓይናቸው የተነሳ ምን ያህል እንዳዝንኩ ስለእኔ ያስባሉ። ባደረጉት ክፋትና ርኩሰት መጸጸታቸው ከፊታቸው ይነበባል። \v 10 ስለዚህም እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ያውቃሉ። ይህን ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ ብዬ አስቀድሜ የተናገርኩት በዓላማ ነው።