\v 6 መሰዊያዎቻችሁ የተጣሉና ባድማ እንዲሆኑ የምትኖሩባቸው ከተሞች ሁሉ የተጣሉ የማምለኪያ ኮረብቶቻቸው ሁሉ ባድማ ይሆናሉ፣ እንዳልነበሩም ሆነው ይጠፋሉ፤ የዕጣን መሰዊያዎቻችሁ ይወገዳሉ ሥራቼሁ ሁሉ ተጠርጎ ይጠፋል። \v 7 የሰዎች ሬሳ በመካከላችሁ ይወድቃል ያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቃላችሁ!