\v 13 ከዚያም ቁጣዬ ይፈጸማል፣ በእነርሱም ላይ የነበረኝ ንዴት ይበርዳል። በእነርሱ ላይ የነበረኝ ንዴቴ በተፈጸመ ጊዜ እኔ እግዚአብሄር በቁጣዬ እንደተናገርኳቸው ያውቃሉ። \v 14 ዙሪያሽን በከበቡሽ አህዛብና በአላፊ አግዳሚው ሁሉ የተዋረድሽና አሳፋሪ አድርግሻለሁ።