\v 26 አመጸኛ ህዝብ ስለሆኑ እንዳትገስፃቸው እኔ ምላስህን ከላንቃህ ጋር አጣብቀዋለሁ አንተም ዲዳ ትሆናለህ። \v 27 ነገር ግን እኔ ስናገርህ አፍህን እከፍታለሁ አንተም ' ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል' ትላቸዋለህ፤ አመጸኛ ህዝብ ስለሆኑ የሚሰማ ይሰማሀል የማይሰማ አይሰማህም!"