am_ezk_text_ulb/03/16.txt

1 line
847 B
Plaintext

\v 16 ከስባት ቀንም በኋላ እንዲህ ሆነ፥ \v 17 "የሰው ልጅ ሆይ አንተን ለእስራኤል ህዝብ እንደጠባቂ አድርጌሀለሁ፥ ስለዚህ የአፌን ቃል ስማና የእኔን ማስጠንቀቂያ ንገራቸው! \v 18 ኃጢአተኛውን ' በእርግጥ ትሞታለህ' ብለህ ንገረው ብዬህ አንተ ግን ባትነግረው ከክፉ መንገዱም እንዲመለስ ባታስጠነቅቀው እርሱ በኃጢአቱ ይሞታል ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ። \v 19 ነገር ግን ኃጢአተኛውን ብታስጠነቅቀው እርሱ ግን ከክፋቱና ከመጥፎ ተግባሩ ባይመለስ በኃጢአቱ ይሞታል አንተም ነፍስህን ታድናለህ።" ብሎ እግዚአብሔር ሲናገረኝ ሰማሁ።