am_ezk_text_ulb/01/01.txt

1 line
636 B
Plaintext

\c 1 \v 1 በሰላሳኛው ዓመት ክአመቱም በአራተኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬብሮን አጠገብ ከምርኮኞቹ ጋር አብሬ እየኖርኩኝ ሳለሁ ሰማያት ተክፍተው የእግዚአብሔርን ራዕይ አየሁ። \v 2 ንጉስ ኢዮአኬም በተማረከበት በአምስተኛው ቀን በከለዳዊያን አገር በኬብሮን ወንዝ አጠገብ \v 3 የእግዚአብሔር ቃል ወደ ካህኑ ወደ ኡዝ ልጅ ወደ ሕዝቅኤል በኃይል መጣ። የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ላይ ነበረች።