am_ezk_text_udb/45/09.txt

4 lines
1.0 KiB
Plaintext

\v 9 \v 10 \v 11 \v 12 9. ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ እናንተ የእስራኤል ገዦች ሕዝብን መበደልና መጨቆን ይብቃችሁ! መልካምና ተገቢ የሆነውን አድርጉ፤ የሕዝቤን ርስት መቀማታችሁንና ከርስታቸው እንዲነቀሉ ማድረጋችሁን ተዉ፡፡
10. በትክክለኛ ሚዛን ተገቢ በሆነ መስፈሪያ ተጠቀሙ፡፡
11. ደረቁን ነገር የምትሰፍሩበት ሚዛንና ፈሳሹን ነገር የምትሰፍሩበት መስፈሪያ ዕኩል ይሁን፤ ደረቅ ነገር ከሆነ ኢፋ በሚባለው መለኪያ ሃያ ሁለት ሊትር፣ ፈሳሽ ከሆነም ባዶስ በሚባለው መስፈሪያ ሃያ ሁለት ሊትር ይሁን፡፡
12. ማንኛውንም ነገር ስትመዝኑ ሁሉም ሰው በሚስማማበት ሚዛን ተጠቀሙ፡፡ አንድ ሰቅል ሃያ ጌራህ የሚይዝ ይሆናል፤ አንድ ምናን ደግሞ ስልሳ ሰቅል ይሆናል፡፡