am_ezk_text_udb/40/22.txt

4 lines
703 B
Plaintext

\v 22 22. መስኮቶቹ፣ መተላለፊያ በረንዳዎቹ፣ የዘብ ቤቶቹና የዘንባባ ዛፍ ጌጦቹ፣ በምሥራቅ በር በኩል ካሉት ጋር ተመሳሳይ ነበሩ፡፡ እንደ ምሥራቁ በር ሁሉ፣ ወደ መተላለፊያ በረንዳው የሚወስዱ ሰባት ደረጃዎች አሉ፡፡
\v 23 23. በምሥራቁ በር እንዳለው ዐይነት በሰሜኑ በር ትይዩ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባ በር ነበረ፤ ከሰሜን በር ጀምሮ ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያመራውን በር ሰውየው ሲለካ ርቀቱ ሃምሳ አራት ሜትር ሆኖ ተገኘ፡፡