am_ezk_text_udb/36/01.txt

6 lines
802 B
Plaintext

\c 36 \v 1 1. ያህዌ ሕዝቅኤልን፣ ‹‹ለእስራኤል ተራሮች ትንቢት ተናገር፤ መልእክቴን እንዲሰሙ ንገራቸው›› አለው፡፡
\v 2 2. በአካባቢው የሚኖሩ የእስራኤል ጠላቶች ኢየሩሳሌም ተደምስሳለች፣ ኮረብታማው አገርና የእስራኤል ተራሮች የእኛ ይሆናሉ በማለት ደስ ብሏቸዋል፡፡
\v 3 3. ስለዚህ እኔ ጌታ ያህዌ የምናገረውን ለእስራኤል ተራሮች ተናገር፣ ‹‹የባዕድ አገር ሕዝቦች ከየአቅጣጫው አጠቋችሁ፤ ወና ሆናችሁ፤ እነዚያ ባዕዳን በምድራችሁ ይኖሩ ጀመር፤ እናንተም የሰዎች መሳቂያና መሳለቂያ ሆናችሁ፡፡