am_ezk_text_udb/30/22.txt

3 lines
780 B
Plaintext

\v 22 22. ስለዚህ ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ላይ ተነሥቻለሁ፤ ታማሚውንና ጤነኛውን ሁለቱን ክንዱን በመሰባበር ከእንግዲህ ሰይፍ እንዳያነሣ የግብፅን ኃይል ፈጽሞ እሰባብራለሁ፡፡
\v 23 23. ግብፃውያንን በሕዝቦች መካከል እበትናለሁ፤ በአገሮችም መካከል እዘራቸዋለሁ፡፡
\v 24 24. የባቢሎንን ንጉሥ ክንድ አበረታሁ፤ ሰይፌንም በእጁ አስይዘዋለሁ፡፡ የግብፅን ክንድ ግን እሰብራለሁ፤ እርሱም ክፉኛ ቆስሎ ሞት አፋፍ ላይ እንዳለ ወታደር በባቢሎን ንጉሥ ፊት ያቃስታል፡፡