am_ezk_text_udb/29/15.txt

2 lines
576 B
Plaintext

\v 15 15. ከመንግሥታት ሁሉ አነስተኛ ትሆናለች፤ በአካባቢው ካሉ አገሮች የበለጠች ታላቅ አገር አትሆንም፡፡ እጅግ ደካማ አደርጋታለሁ፤ ከእንግዲህ ሌሎች አገሮችን መግዛት አትችልም፡፡
\v 16 16. በዚያ ጊዜ እስራኤላውያን ግብፅ እንድትረዳቸው መጠየቅን አያስቡም፡፡ በዚያ ጊዜ ጌታ ያህዌ አደርጋለሁ ያለውን የማድረግ ኃይል እንዳለው የእስራኤል ሕዝብ ያውቃል፡፡