\v 24 ረጃጅም ዛፎችን የማስወግድ፣ ትንንሾቹን የማሳድግ እኔ ያህዌ መሆኔን የዱር ዛፎች ሁሉ ያውቃሉ፡፡ የለመለመውን ትልቅ ዛፍ አጠወልጋሁ፣ የደረቀውንም ዛፍ አለመልማለሁ፡፡ እኔ ያህዌ ይህን ተናግሬአለሁ፤ የተናገርሁትም በእርግጥ ይፈጸማል፡፡