am_ezk_text_udb/38/07.txt

1 line
887 B
Plaintext

\v 7 ለጐግ እንዲህ በለው፤ በዙሪያህ ለተሰበሰቡት ወታደሮች ሁሉ መሪያቸው ሁን፡፡ \v 8 ከብዙ ጊዜ በኃላ በጦርነት ከወደሙ በኃላ ያገገመችውን ሕዝቧ ከአያሌ አሕዛብ መካከል ወጥቶ የተሰበሰበውን፣ ለብዙ ጊዜ ባድማ በነበረው ተራራ ላይ የሰፈረውን አገር እስራኤልን ለመውረር እነዚህን ወታደሮች ይዘህ እንድትዘምት አዝዝሃለሁ፡፡ ከሕዝቦች መካከል ወጥተው አሁን ሁሉም በሰላም እየኖሩ ነው፡፡ \v 9 አንተና አብረውህ ያሉት ከብዙ አገሮች የተሰባሰበው ሰራዊት፣ እንደ ታላቅ ማዕበል ወደ እስራኤል ትመጣላችሁ፤ ሰራዊትህ ምድርን እንደሚሸፍን ደመና ይሆናል፡፡