am_ezk_text_udb/40/28.txt

8 lines
1.1 KiB
Plaintext

\v 28 28. ከዚያም በደቡብ በኩል ባለው መግቢያ ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ የደቡብንም በር ለካው፤ መጠኑም ከሌሎች በሮች ጋር ተመሳሳይ ሆነ ተገኘ፡፡
\v 29 29. የዘብ ቤቶቹን፣ መከለያ ግድግዳዎቹንና መተላለፊያ በረንዳዎቹን ለካ፤ መግቢው በርና መተላለፊያ በረንዳው ዙሪያውን መስኮቶች ነበሩዋቸው፡፡ መግቢያው በርና መተላለፊያ በረንዳው ሃያ ሰባት ሜትር ርዝመት፣ 13.5 ስፋት ነበራቸው፡፡
\v 30 30. ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያደርሰው የውስጠኛው መተላለፊያ በረንዳ በር 13.5 ርዝመት 2.7 ሜትር ስፋት ነበረው፡፡
\v 31 31. የመተላለፊያ በረንዳው መግቢያ ከውጫዊው አደባባይ ትይዩ ነበር፡፡ ግድግዳዎቹ በዘንባባ ዛፎች ቅርጽ አጊጠው ነበር፤ ወደዚያ የሚያደርሱ ስምንት በሮች ነበሩ፡፡