|
\v 5 5. ስለዚህም ያ ዛፍ ደን ውስጥ
|
|
ካሉት ዛፎች ሁሉ እጅግ ከፍ አለ
|
|
ቅርንጫፎቹ በዙ፤ ቀንበጦቹ ረዘሙ
|
|
ከውሃው ብዛት የተነሣ ተስፋፉ፡፡
|
|
\v 6 6. ቅርንጫፎቹ ላይ ወፎች ጐጆአቸውን ሠሩ
|
|
አራዊትም ከቅርንጫፎቹ ሥር ግልገሎቻቸውን ወለዱ
|
|
የታላላቅ መንግሥታት ሕዝቦች በጥላው ሥር ያርፉ ነበር፡፡
|
|
\v 7 7. ሥሮቹ ብዙ ውሃ ወዳለበት ጠልቀው ስለ ነበር
|
|
ከተንሰራፉት ቅርንጫፎቹ ጋር
|
|
ዛፉ እጅግ ያማረና ባለ ግርማ ሆነ፡፡ |