am_ezk_text_udb/40/32.txt

6 lines
916 B
Plaintext

\v 32 32. ከዚያም ሰውየው በምሥራቅ በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ መግቢያ በሩንም ለካው፣ መጠኑም ከሌሎች በሮች ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡
\v 33 33. የዘብ ቤቶቹ፣ መከለያ ግድግዳዎቹና መተላለፊያ በረንዳዎች መጠን ከሌሎቹ ጋር ተመሳሳይ ነበር፡፡ መግቢያ በሩና መተላፊያ በረንዳው ዙሪውን መስኮቶች ነበሩዋቸው፡፡ መግቢያ በሩና መተላለፊያው በረንዳ ሃያ ሰባት ሜትር ርዝመትና 13.5 ሜትር ስፋት ነበሩዋቸው፡፡
\v 34 34. በረንዳው ከውጫዊው አደባባይ ትይዩ ነበር፤ ይኸኛውም በዘንባባ ዛፍ ቅርጽ ያጌጡ ግድግዳዎች ነበሩት፤ ወደዚያ የሚያደርሱ ስምንት ደረጃዎችም ነበሩ፡፡