am_ezk_text_udb/27/16.txt

3 lines
888 B
Plaintext

\v 16 16. ብዙ የሸቀጥ ነገሮች ስለ ነበሩሽ የሶርያ ሰዎች የንግድ ሸቀጥሽን ሁሉና ሌሎችንም ብዙ ዕቃዎች ይገዙሽ ነበር፤ በወሰዱትም ምትክ በሉር፣ ሐምራዊና በጥልፍ ያጌጠ ልብስ፣ ቀጭን ሐር፣ ከዛጐል የተሠሩ ጌጣጌጦችና ቀይ ዕንቁ ይሰጡሽ ነበር፡፡
\v 17 17. የይሁዳና የእስራኤል ሰዎች ለሸቀጥሽ ዋጋ በአሞን ካለው የሚኒት አገር ስንዴ፣ በለስ፣ ማር፣ የወይራ ዘይትና ቅመማ ቅመም ይከፍሉሽ ነበር፡፡
\v 18 18. ብዙ የምትሸጫቸውና የምትገዣቸው ነገሮች ስለ ነበሩ ደማስቆ የኬብሎንን የወይን ጠጅና የዛሐርን ነጭ የበግ ጠጉር በማቅረብ ከአንቺ ጋር ተገበያይታለች፡፡