am_ezk_text_udb/22/01.txt

1 line
630 B
Plaintext

\c 22 \v 1 ያህዌ ሌላም መልእክት ሰጠኝ፤ እንዲህም አለኝ፤ \v 2 የሰው ልጅ ሆይ፣ በነፍስ ገዳዮች በተሞላችው በኢየሩሳሌም ከተማ ለመፍረድ ተዘጋጅተሃልን? የፈጸሙትን ርኩሰት ሁሉ አስታውሳቸው፡፡ \v 3 እንዲህም በላቸው፤ ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ‹ሰዎችን በመግደል፤ ራሳችሁንም በማርከስ፣ ለራሳችሁ ጣዖቶች በማበጀት፣ እናንት የዚህች ከተማ ሰዎች እኔ እንዳጠፋችሁ ራሳችሁን አዘጋጅታችኃል፡፡