\v 3 ጌታ ያህዌ ግን እንዲህ ይላል መረብ እንዲዘረጉብህ ብዙ ሕዝብ እልክብሃለሁ እየጐተቱም ወደ ምድር ያወጡሃል፡፡ \v 4 መሬትም ላይ ይጥሉሃል፤ ሜዳም ላይ ይዘረጉሃል፤ የሰማይ ወፎችም እንዲሰፍሩብህ አደርጋለሁ የምድረ አራዊትም ሁሉ እስኪጠግቡ ይበሉሃል፡፡