diff --git a/20/23.txt b/20/23.txt new file mode 100644 index 0000000..0edb0a6 --- /dev/null +++ b/20/23.txt @@ -0,0 +1,2 @@ +\v 23 23. ስለዚህ በአሕዛብ መካከል እንደምበትናቸውና ወደ ተለያዩ አገሮች እንደማፈልሳቸው በምድረ በዳ እጄን አንሥቼ በፊታቸው ማልሁ፡፡ +\v 24 24. ምክንያቱም ሕጌን ስለ ተላለፉ፣ ሥርዐቴንም ስላልተከተሉ፣ ሰንበቴን እንደ ሌላው ቀን ስላደረጉና አባቶቻቸው ሲያመልኳቸው ከነበሩ ጣዖቶች ጋር ስለ ተጣበቁ ነው፡፡ \ No newline at end of file diff --git a/20/25.txt b/20/25.txt new file mode 100644 index 0000000..33e12d0 --- /dev/null +++ b/20/25.txt @@ -0,0 +1,2 @@ +\v 25 25. እኔም መልካም ላልሆነ ሥርዐትና በሕይወት ለማይኖሩበት ሕግ አሳልፌ ሰጠኃቸው፡፡ +\v 26 26. እኔ ያህዌ የተናገርሁትን የማድረግ ኃይል ያለኝ መሆኑን እንዲያውቁ አስደነግጣቸው ዘንድ በእሳት በሚያቀርቡት የበኩር ልጅ መሥዋዕት እንዲረክሱ አደረግኃቸው \ No newline at end of file diff --git a/20/27.txt b/20/27.txt new file mode 100644 index 0000000..5efb3d3 --- /dev/null +++ b/20/27.txt @@ -0,0 +1,3 @@ +\v 27 27. ስለዚህ የሰው ልጅ ለእስራኤል እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ ‹አባቶቻችሁ ከእኔ ወደ ጣዖቶች ዘወር በማለታቸው አቃለሉኝ፡፡ +\v 28 28. ወደ ማልሁላቸው ምድር ካመጣሁዋቸው በኃላ ከፍ ያለ ኮረብታ ወይም ለምለም ዛፍ ባዩ ቁጥር በዚያ ለጣዖቶች መሥዋዕት አቀረቡ፤ ቁርባናቸውንም በማቅረብ ቁጣዬን አነሳሡ፡፡ መልካም መዐዛ ያለውን ዕጣናቸውን ዐጠኑ፤ የመጠጥ ቁርባናቸውንም አፈሰሱ፡፡ +\v 29 29. እኔም በዚህ ኮረብታ እንድታመልኩ የነገራችሁ ማን ነው? በማለት ጠየቅሁዋቸው ይህ ቦታ እስከ ዛሬም ድረስ ባማ ተብሎ ይጠራል፤ ትርጒሙም፣ ‹‹የኮረብታ ማምለኪያ›› ማለት ነው፡፡ \ No newline at end of file diff --git a/20/30.txt b/20/30.txt new file mode 100644 index 0000000..7f66220 --- /dev/null +++ b/20/30.txt @@ -0,0 +1,3 @@ +\v 30 30. ስለዚህ ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በል፤ ‹ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ አባቶቻችሁ እንዳደረጉ የምታደርጉት ለምንድነው? ባልዋን ትታ ከሌላ ወንድ ጋር እንደምታመነዝር ሴት እኔን ትታችሁ የረከሱ ጣዖቶች አምልካችኃል፡፡ +\v 31 31. ልጆቻችሁን በእሳት መሥዋዕት አድርጋችሁ በማቅረብ ረክሳችኃል፡፡ እናንተ እስራኤላውያን፣ ታዲያ፣ የእኔን ሐሳብ እንድትጠይቁ ልፍቀድላችሁን? በሕያውነቴ እምላለሁ እንድትጠይቁኝ አልፈቅድም ይላል ጌታ ያህዌ፡፡ +\v 32 32. እናንተም፣ ‹‹በዓለም ውስጥ እንዳሉ ሌሎች ሕዝቦች እንሆናለን፤ እነርሱ እንደሚያደርጉት ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩ ጣዖቶችን እናመልካለን›› አላችሁ፡፡ ነገር ግን ያሰባችሁት ከቶ አይሆንም፡፡ \ No newline at end of file diff --git a/20/33.txt b/20/33.txt new file mode 100644 index 0000000..1942e42 --- /dev/null +++ b/20/33.txt @@ -0,0 +1,3 @@ +\v 33 33. በሕያውነቴ እምላለሁ ይላል ጌታ ያህዌ፤ በብርቱ ክንድና በተዘረጋች እጅ መዓትን በማፍሰስ በላያችሁ እነግሣለሁ፡፡ +\v 34 34. በታላቅ ኃይሌ እናንተን ከበተንሁበት ምድር እሰበስባችኃለሁ፡፡ +\v 35 35. ወደ አሕዛብ ምድረ በዳ አመጣችኃለሁ፤ በዚያም ፊት ለፊት ከእናንተ ጋር እፋረዳለሁ፡፡ \ No newline at end of file diff --git a/20/36.txt b/20/36.txt new file mode 100644 index 0000000..8b1ca39 --- /dev/null +++ b/20/36.txt @@ -0,0 +1,3 @@ +\v 36 36. ግብፅ አጠገብ ባለው ምድረ በዳ አባቶቻችሁን እንደ ቀጣሁ እናንተንም እቀጣችኃለሁ፡፡ +\v 37 37. እንድትገዙልኝ አደርጋለሁ፤ ከእናንተ ጋር ላደረግሁት ኪዳን እንድትታዘዙ አስገድዳችኃለሁ፡፡ +\v 38 38. በእኔ ላይ ያመፁትን በመካከላችሁ ያሉትን ሰዎች አስወግዳለሁ፡፡ አሁን ካሉበት ባቢሎን ባወጣቸው እንኳ ወደ እስራኤል ምድር አይገቡም፡፡ በዚያ ጊዜ እኔ ያህዌ የተናገርሁትን የማድረግ ኃይል እንዳለኝ ታውቃላችሁ፡፡ \ No newline at end of file diff --git a/20/39.txt b/20/39.txt new file mode 100644 index 0000000..81fbc85 --- /dev/null +++ b/20/39.txt @@ -0,0 +1 @@ +\v 39 39. የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፣ ስለ እናንተ ግን ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ የማትሰሙኝ ከሆነ፣ እያንዳንዳችሁ ሂዱና ለጣዖቶቻችሁ ስገዱ፤ ከዚያ በኃላ በእርግጥ ትሰሙኛላችሁ፤ ቁርባናችሁን ለጣዖቶቻችሁ በማቅረብም ከእንግዲህ እኔን አታቃልሉም፡፡ \ No newline at end of file diff --git a/20/40.txt b/20/40.txt new file mode 100644 index 0000000..cdd4048 --- /dev/null +++ b/20/40.txt @@ -0,0 +1,2 @@ +\v 40 40. ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፤ በእስራኤል ከፍ ባለው ቅዱስ ኮረብታ በጽዮን ስጦታ ይዛችሁ ትመጣላችሁ፤ ስጦታችሁንና በኩራታችሁን ከተቀደሱ መሥዋዕቶቻችሁ ሁሉ ጋር በዚያ እሻለሁ፡፡ +\v 41 41. ተበታትናችሁ ከነበራችሁበት አገሮች ሕዝቦች መካከል አውጥቼ በምሰበስባችሁ ጊዜ መልካም መዐዛ እንዳለው ዕጣን እቀበላችኃለሁ፡፡ ሌሎች ሕዝቦች እያዩ በእናንተ መካከል ቅድስናዬን እገልጣለሁ፡፡ \ No newline at end of file diff --git a/20/42.txt b/20/42.txt new file mode 100644 index 0000000..2240207 --- /dev/null +++ b/20/42.txt @@ -0,0 +1,3 @@ +\v 42 \v 43 42. ለአባቶቻችሁ ወደ ማልሁላቸው ወደ እስራኤል ምድር ሳመጣችሁ ያንን ያደረግሁ እኔ ያህዌ መሆኔን ታውቃለችሁ፡፡ +43. የፈጸማችኃቸውን አሳፋሪ ነገሮችና ራሳችሁንም እንዴት እንዳረከሳችሁ በዚያ ቦታ ታስተውላላችሁ፡፡ +\v 44 44. እስራኤላውያን ሆይ፣ እንደ ክፉ መንገዳችሁና እንደ ብልሹ ተግባራችሁ ሳይሆን፣ ስለ ስሜ ስል በምጐበኛችሁ ጊዜ እኔ ያህዌ የተናገርሁትን እንደማደርግ ታውቃላችሁ ይላል ጌታ ያህዌ፡፡ \ No newline at end of file