am_eph_text_ulb/03/03.txt

1 line
542 B
Plaintext

\v 3 ቀደም ሲል እንደጻፍሁላችሁ እግዚአብሔር የተሰወረውን ምስጢር በመገለጥ እንዳውቅ አድርጓል። \v 4 ይህን በምታነቡበት ጊዜ ስለ ክርስቶስ ምስጢር እኔ ያለኝን መረዳት መገንዘብ ትችላላችሁ። \v 5 ምስጢሩም አሁን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ለሓዋርያቱ እና ለነቢያቱ የተገለጠው ያህል ባለፉት ዘመናት ለነበሩ ሰዎች አልተገለጠም ነበር።