am_eph_text_ulb/02/13.txt

1 line
946 B
Plaintext

\v 13 ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር ርቃችሁ የነበራችሁት በክርስቶስ ኢየሱስ በመሆን በክርስቶስ ደም አማካይነት ወደ እግዚአብሔር እንድትቀርቡ ተደርጋችኋል። \v 14 አይሁድንና አሕዛብን ሁለቱን አንድ ሕዝብ ያደረገ እርሱ ሰላማችን ነውና ፤ በሥጋውም እርስ በርስ የለያየንን የጥል ግድግዳ አፈረሰ። \v 15 ይኸውም ከሁለቱ ሕዝቦች አንድ አዲስ ሕዝብ በመፍጠር ሰላምን ያደርግ ዘንድ የትእዛዛትንና የሕግ ደንቦችን በሥጋው ሻረ። \v 16 ይህንንም ያደረገው በመስቀሉ አማካይነት በመካከላቸው የነበረውን ጠላትነት ገድሎ ሁለቱን ሕዝቦች አንድ አካል በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ነው።