am_eph_text_ulb/01/19.txt

1 line
733 B
Plaintext

\v 19 እንዲሁም እንደ ኀይሉ ብርታት አሠራር በእኛ በምናምነው ውስጥ የሚሠራው የኀይሉ ታላቅነት ምን እንደሆነ እንድትረዱ ነው። \v 20 ይህም እግዚአብሔር ከሙታን ባስነሳውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ እንዲቀመጥ ባደረገው ጊዜ በክርስቶስ ውስጥ የታየው ኀይል ነው። \v 21 ክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በአብ ቀኝ የተቀመጠውም ከማንኛውም ግዛት፥ ሥልጣን፥ኀይልና ጌትነት እንዲሁም በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚችለው ስም ሁሉ በላይ ነው።