am_ecc_text_udb/04/07.txt

1 line
879 B
Plaintext

\v 7 በምድር ላይ ስለሚከናወን ስለ ሌላም ከንቱ ነገር አሰብሁ። \v 8 ያም ብቻቸውን ስለሚኖሩ ሰዎች ነው። እነዚህ ሰዎች አብሮአቸው የሚኖር ቤተ ሰብ ወይም ልጆች ወይም ወንድሞችም ሆኑ እህቶች የሏቸውም። ሳያቋርጡ ሁልጊዜ ተግተው በመሥራት ብዙ ገንዝብ ያገኛሉ። ነገር ግን በሚያገኙት ነገር ፈጽሞ አይረኩም። ራሳቸውንም እንዲህ በማለት ይጠይቃሉ፡« ሥራ በመሥራት ብዙ የምለፋው ለምንድን ነው? ማንንስ ለመርዳት ብዬ ነው? ማድረግ ደስ የሚለኝን ነገር የማላደርገው ለምንድን ነው? እስካሁን እያደረግሁት ያለው ነገር ከንቱ ነው» ይህም በጣም መጥፎ ነው።