am_dan_text_ulb/08/07.txt

1 line
608 B
Plaintext

\v 7 እየወጋውና ሁለቱን ቀንዶቹን እየሰበረ፣ በጭካኔ አውራውን በግ ሲጎዳው አየሁ፤ አውራ በጉም ለመቋቋም ጉልበት አልነበረውም። ፍየሉ በምድር ላይ ጥሎ ረገጠው፤ አውራ ብጉንም ከፍየሉ እጅ ለማዳን የሚችል አልነበረም። \v 8 ፍየሉም ታላቅ ሆነ፤ ነገር ግን በኃይሉ በበረታ ጊዜ፣ ትልቁ ቀንዱ ተሰበረ፤ በቦታውም ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት የሚያመለክቱ አራት ታላላቅ ቀንዶች በቀሉ።