am_dan_text_ulb/10/20.txt

1 line
474 B
Plaintext

\v 20 እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “ለምን ወደ አንተ እንደ መጣሁ ታውቃለህ? የፋርስን መንግሥት ለመውጋት እመለሳለሁ፤ እኔም ስሄድ የግሪክ አለቃ ይመጣል። \v 21 አስቀድሜ ግን በእውነት መጽሐፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ ከእነዚህ አለቆች ጋር ለመዋጋት ከአለቃችሁ ከሚካኤል በስተቀር የሚረዳኝ የለም።