am_dan_text_ulb/09/17.txt

1 line
781 B
Plaintext

\v 17 አሁንም አምላካችን ሆይ፣ የአገልጋይህን ጸሎትና ልመና ስማ። ጌታ ሆይ፤ ስለ ስምህ ስትል ፊትህን ወደፈረሰው መቅደስ መልስ። \v 18 አምላክ ሆይ፤ ጆሮህን አዘንብለህ ስማ፣ ዐይንህን ገልጠህ መጥፋታችንንና ስምህ የተጠራበትን ከተማ ተመልከት። ልመናችንን የምናቀርበው ስለ ጽድቃችን ሳይሆን፣ ስለ ታላቅ ምሕረትህ ነው። \v 19 ጌታ ሆይ፣ አድምጥ! ጌታ ሆይ፤ ይቅር በል! ጌታ ሆይ፤ ስማ! አድርግም፤ ስምህ በከተማንህና በሕዝብህ ላይ ተጠርቶአልና አምላኬ ሆይ፣ ስለ ስምህ ስትል አትዘግይ።”