\v 5 እኛ ኃጢአት ሠርተናል፣ በድለናልም፣ ክፋትን አድርገናል፣ ዐምፀናልም፣ ከትእዛዝህና ከሕግህ ዘወር ብለናል። \v 6 ለንጉሦቻችን፣ ለልዑሎቻችንና ለአባቶቻችን እንዲሁም ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉ በአንተ ስም የተናገሩትን አገልጋዮችህን ነቢያትን አልሰማንም።