am_dan_text_ulb/07/13.txt

1 line
497 B
Plaintext

\v 13 ሌሊት ባየሁት ራእይ የሰውን ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመና ጋር ሲመጣ አየሁ፤ ወደ ጥንታዌ ጥንቱ መጣ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት። \v 14 14 ሥልጣን፣ ክብርና ታላቅ ኃይል ተሰጠው፤ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች፤ መንግሥታትና ሕዝቦች ሰገዱለት፤ ግዛቱም ለዘላለም የማያልፍ ነው፤ መንግሥቱም ፈጽሞ የማይጠፋ ነው።