am_dan_text_ulb/07/06.txt

1 line
787 B
Plaintext

\v 6 ከዚህ በኋላ ተመለክትሁ፤ በፊቱ በኩል ነብር የሚመስል ሌላ አውሬ ነበር፤ በጀርባውም በኩል የወፍ ክንፍ የሚመስሉ አራት ክንፎች ነበርት፤ ይህ አውሬ አራት ራስ ነበረው፤ ለመግዛትም ሥልጣን ተሰጠው። \v 7 ከዚህ በኋላ በሌሊት ራእይ አየሁ፤ በፊቴም የሚያስፈራና የሚያስደነግጥ በጣም ኃይለኛ የሆነ አራተኛ አውሬ ነበር፤ ትልቅ የብረት ጥርሶች ነበሩት፤ ያደቅና ይበላ፣ የቀረውንም ሁሉ በእግሮቹ ይረጋግጥ ነበር። ከእርሱ በፊት ከነበሩት አራዊት ሁሉ የተለየ ሲሆን፤ አሥር ቀንዶች ነበሩት።