\v 3 ጥበበኞች እንደ ሰማይ ጸዳል፣ ብዙዎችንም ወደ ጽድቅ የሚመልሱ እንደ ክዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ። \v 4 ዳንኤል ሆይ፣ አንተ ግን፣ እስከ ፍጻሜው ዘመን ድረስ የመጽሐፉን ቃል ዝጋ አትመውም። ብዙዎች ወዲያ ወዲህ ይራወጣሉ ዕውቀትም ይበዛል።