\c 10 1 የፋርስ ንጉስ ቂሮስ በነገሰ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ዳንኤል ራዕይ ታየው መልዕክቱ እውነት ነው፤ ስለ ታላቅ ጦርነትም የሚገልፅ ነበር፡፡ መልእክቱንም ይገነዘብ ዘንድ በራዕዩ ማስተዋል ተሰጠው፡፡